
ቅኔ ልቀኝልሽ ከአዳም ግራ ጎን ገላሽ የተበጀው እንደ ስሕተት ዛፍ ስንቱን አስጎመጀው የጎመራው ጡትሽ እንደበለስ ፍሬ ችምችም ዞማ ጠጉርሽ 'ጆንትራ' ጎፈሬ ባራቱ ቅኝቶች ተዜመልሽ ዜማ የውበትሽ ንግርት ባገሩ ተሰማ ተውረግራጊው ዳሌሽ ስንት ተባለለት አብረቅራቂው ጥርስሽ ብሩህ ቀን ወጣለት ማዲንጎ ታምራት ጥሌን አዘዘለት! አሁን በዘመኔ እኔም ላዚምልሽ ቅኔ ልቀኝልሽ..... እንደ ኤፍራጥስ ወንዝ ተፈጥሮሽ ነጠፈ ዋናውን ዘንግቶ ሰውሰራሽ ለጠፈ ሽፋሽፍት ተገዛ ?ጥፍር ተሸመተ ለገላሽ መተኪያ እቃ ተመረተ ጠጉርሽ ወርዶ ወርዶ ባትሽን አለፈው ሰው አገኘሁ ብሎ እየዘረገፈው

