[Intro] [acoustic guitar riff, shaker, hand drum] [Verse 1] [male vocals] አለመታደሌ አንቺ ላይ ጥሎኛል ልቤን ተቀምጬ ሰው ሰው ያሰኘኛል ሆድ ካገር ይሰፋል እችለዋለሁኝ አምላክ ካልፈቀደ ምን አመጣለሁኝ ሞኝ ነኝ ተላላ እጅግ ደግ ሰው ፍቅር አገኝ ብዬ ልቤን የምሰጠው እናቲየው ናቸው ጥፋት ያጠፉት ሰው ወለድኩኝ ብለው ፈጠሩ መላክት መልኳን አሳምረው ተጥበው ሲወልዷት ከመልኳ ቀንሰው ፀባይ ቢለግሷት ምን አለ ከመልኳ ቀንሰው ፀባይ ቢለግሷት [Chorus] ሁሉም ሰው ይለኛል ምን ሆኗል ይሄ ሰው እንደኔ ደርሶበት ፍቅሯን አልቀመሰው አንቺን ያገኘሁ ለት መታደል መስሎኛል አለመታደሌ እድሌ አንቺ ላይ ጥሎኛል [Verse 2] አንቺ አስከፍተሽኝ ከአምላክ ተጣልቼ ከዘመድ ጓደኛ ከሰው ተለይቼ አንጎራጉራለሁ ቤቴ ተዘግቼ በትዝታ ስንቅ ትዝታም ስንቅ ነው ሲያልፍ እያስታወሱ አሮጌ ይረሳል ሲተካ በአዲሱ እንጉርጉሮ ዜማ ቅኝት ተቀኝቼ አንቺም ተቆጭተሽ እኔም ተቆጭቼ ለማይሆን ነገር ቆጭኝ መቆጨቴ ለማይሆን ነገር ቆጭኝ መቆጨቴ [Verse 3] አንቺን አክሽኝ እንጂ አምላክ ይወደኛል የሚያፈቅር የሚወድ ጥሩ ልብ ሰጥቶኛል ትልቁ ሰውዬ የተከበርኩት ባንቺ አይደል በሰው ፊት የተዋረድኩት አላት ምናምን ነገር ያለችውን ሁሉ እሺ የሚያስብል ፍቅሯን የቀመሰው አይመልሰውም ሰው አምላኩን ረስቶ እያመለከ ሰው እግዚአብሔር ይሁነው እሷን የወደደ የቀመሳት ሁሉ ጨርቁን ጥሎ አበደ የቀመሳት ሁሉ ጨርቁን ጥሎ አበደ