
ሰሌዳውን ፋቀው፣ ቀለም መቁጠሪያህን፣ ታገልና ስበር ያን መቀመጫህን፣ በግድግዳውም ላይ ነውርህን ፃፍበት፣ ሰርዝበት፣ ደልዝበት፣ ተፈላሰፍበት፣ የእጅህን ቆሻሻ እድፉን አብስበት፡፡ በሚስማር ፈርፍረህ፣ በምላጭም ፋቀው፣ ስምህን ፃፍበት በቀለም ለቅልቀው፣ ቆመህ ተላፋበት “ዴስክህን˚ አንክተው፡፡ መስኮት፣ መስተዋቱ፣ መብራቱ እንዲራገፍ፣ ምሶሶው፣ መቃኑ፣ ማገሩ እንዲዛነፍ፣ እግረ ተሜ በርታ ክፍልህን አፍርሰው፣ በወግ ተጠብቆ ለትውልድ ባያልፍ ላንተ ጉዳይህ ነው

