መሰላል ለመውጣት አለው ትልቅ ብልሀት፡፡ የላዩን ጨብጦ፣ የታቹን ረግጦ፣ ወደ ላይ መመልከት እጆችን ዘርግቶ በሀይል መንጠራራት፡፡ ጨብጦ መጐተት የላዩን፣ ላዩ ታች እንዲሆን፡፡ አንድ በአንድ እየረገጡ መሰላል የወጡ፣ ብልሆች የማይጣደፉ ሞልተዋል በያፋፉ፡፡ ዘርግተው የጨበጡትን መርገጥ የመውጣት ሕግ ነው የማይለወጥ፡፡ .... ሲወርዱ ግን ያስፈራል የረገጡትን ያስጨብጣል፡፡ የረገጡትን ያስጨብጣል፡፡ የረገጡትን ያስጨብጣል፡፡ የረገጡትን ያስጨብጣል፡፡