Song Cover Image

እንዳይነግርህ አንዳች እውነት

ደንስ ጎበዝ ደንስ ጀግና ክራቫትክን አውልቅና ሀሳብክን ልቀቀውና ኮትክን ሸሚዝክን ጣልና ርገጥ፣ ጨፍር፣ ደንስ ጀግና፡፡ ያን የሙዚቃ ናዳ የኮንትራባሱን መብረቅ ልቀቀውና ይድብለቅለቅ ምድር በሆይታ ይጥለቅለቅ፡፡ ምንም ምንም እንዳታስብ፣ ሁሉን ሁሉን እንድትረሳ ደንስ ካካታው ይረሳ ጨፍር፣ ወለሉ እስኪበሳ፡፡ ሃይ-ሃይ! ዋይ! ሃይ-ሃይ በልበት የጃዝ ፈንፋር አንኳኳበት ራስክን እንዳታስብበት፡፡ ሆ! በል! እሪ! በል ምታበት ፎክርበት፣ አቅራራበት አናፋበት፣ ሸልልበት የሲቃ ሳቅ አስካካበት ሆያ- ሆዬ በል ጩህበት፣ ኡኡታህ፣ መንኮራኩርክን እስኪያሰጥመው አጓራበት ጭንቅላትክን ግዘፍበት፣ ውቀጥበት ውገርበት .. ዝግ ብሎማ ያሰበ እንደሁ፧ ይነግርሀል አንዳች እውነት፡፡