Song Cover Image

ምን ያደርጋል

ምን ያደርጋል ሀገር፣ …. ምን ሊበጅ ዜግነት፣ ወልደው ካልሳሙበት፣ …. ዘርተው ካልቃሙበት፣ ህጻናት በመስኩ፣ …. አዛውንት በሸንጎ፣ …. ደምቀው ካልታዩበት፣ እምቦሳን በጓሮ፣ …. ጥገትቱን ከጨፌው፣ … ታስረው ካልዋሉበት፣ ጋማ ከብቱ በመስክ፣ … አውሬም በውርማ፣ … ሞልተው ካልታዩበት፣ ፏፏቴው በዳገት፣ … ጅረት በሸለቆ፣ … ሲፎክር ካልሰሙት፣ ተራራውም በደን፣ … ክምሩ ባውድማ፣ …. ገኖ ካልታየበት። ምንያደርጋል ሀገር ……? ከሰው ተወዳጅተው፣ … ከሰው ተዋውለው፣ …. ህይወት ካልመሩበት፣ ቅጠሉን በጥሰው፣ … አፈሩንም ልሰው፣ …. ቆመው ካልሄዱበት፣ አርሰው፣ አሳርሰው፣ …. ነግደው፣ አትርፈው … ሐብት ካልደረጀበት፣ ከእውቀትም ጨልፈው፣ … በሳይንስ ተራቀው፣ … ለድገት ካልሰሩበት፣ እናቶች፣ ህጻናት፣ … መበለት፣ አዛውንት፣ … ካልተከበሩበት፣ ታመው ካልዳኑበት፣ … አርጅተው አፍጅተው፣ … ካልተቀበሩበት። ወጥተው ካልገቡበት፣ …. ሰርተው ካልኖሩበት፣ ከሸንጎው ዳኝነት፣ …. ከወንበሩ ፍትህ፣ …. ነጥፈው ከጠፉበት፣ መብት ሚዛን አጥቶ፣ …. ስርዓት ባገር ጠፍቶ፣ … እብሪት ከገዛበት፣ ዜግነት ከሀገር፣ …. ማንነት ከአንድነት፣ …. ሰላም ከመቻቻል፣ … ከተለያዩበት፣ ባሳብ ተደራጅተው፣ … ደግፈው ተቃውመው፣ … ውለው ካልገቡበት፣ በልዩነት ደምቀው፣ … በባህል፣ በእምነት፣ … ካልተከበሩበት። ምን ያደርጋል ሀገር ……? መውጣትና መግባት፣ …. መኖርና መስራት፣ … ከሚያስጨንቁበት፣ ያገር መውደድ ፍቅር፣ …. ነጻነት፣ አርነት፣ … ወንጀል ከሆነበት፣ ቃዬል በመንበሩ፣ … ይሁዳ ከልፍኙ፣ … ከሰለጠኑበት . ዜጋው ጠላት ሆኖ፣ … ዘራፊና ባእድ፣ …. ተከብረው ካሉበት፣ ስደትና ረሀብ፣ …. እስራትና ሞት፣ …. ዳረጎት ከሆኑት፣ በስልጣን መባለግ፣ …. በሀብት መንደላቀቅ፣ … ገነው ከታዩበ