
የተለየህ ፍጡር አንተ ቀሰስተኛ ' ለምን ትሆናለህ ሁሌ መንገደኛ ? ጉዞህ ረዥም ነው መድረሻህም ሩቅ ፡ እንቅፋት ቢኖርም አታውቅም መጨነቅ ። አየሁህ ስትጓዝ አቋርጠህ በመስኩ ፡ አሰብኩ ልከተልህ ላውቅህም ፈለግኩ ። በቀስታ ጉዞህ ከመገረም በቀር ' ጊዜ አላገኘሁም ብዙ ልመራመር ። ሣሩ አድጐ ከፊትህ ሲወፍር ' ሲረዝም ፡ ትንጠላጠላለህ አስተኝተህ አግድም፡ « ተራራ እምትወጣ እንዲህ ቤትህን አዝለህ ፡ እምታስተምረኝ ምንድን ጥበብ አለህ ? » ብዬ ብጠይቅህ መልስህ የዝምታ' እንቆቅልሽ ሆነ ውሉ እማይፈታ ። ምክሬን ላካፍልህ ወዳንተ ብል ጐንበስ' ቤትህ ገባህና ዘግተህ ላትል ቅስቅስ ። ጥቅልል ብለህ ተኛህ ስሔድ ልትንፏቀቅ ነገ አገኝህ የለ ስንዝር እንኳ ሳትርቅ !

